top of page

BUSINESS NEWS

የኢትዮጵያውያን  የስፖርትና የባሕል ፌስታል ፥ እንግዶች ፥

ሊያውቋቸው የሚገቧቸው ፥ ፯ቱ የጆርጅያ ሕጎችና አንድምታቸው

Seven Georgia Laws that 2019 Visitors Need to Know

ATLANTA, GA —የኢትዮጵያውያንን የስፖርትና የባሕል ፌስታል ፥ በምታስተናግደው ፥ አትላንታ ፡ ጆርጅያ ፡ ሲቆዩ ፥ የሚከተሉትን ሕግ ነክ ቁምነገሮች ፥ ሊያውቁና ሊጠነቁ ግድ ይልዎታል፤

  1. እጅዎን ፥ ከተንቀሳቃሽ ስልክዎ ያርቁ፦   HANDS-FREE LAW | በጋራ ወይም በሕዝብ ትራንስፖርት መጠቀም ሳይችሉ ቀርተው ፥ መኪና ለማሽከርከር ቢገደዱ ፥ ስልክዎን በእጅዎም ሆነ በማንኛውም የአካልዎ ክፍል መንካት አይችሉም። ስልክዎን በእጅዎ ይዘው፣ ወይም ከጆሮዎ  ለጥፈው ከተያዙ ፥ ፖሊስ ቲኬት ይሰጥዎታል፤ እንደ ታሪክዎ ሁናቴ ፥ ከ፩ እስከ ፫ ነጥብና የገንዘብ ቅጣትም ይጠብቅዎታል፤ “ያላረፈች  ጣት ማለት፥ ይሄኔ ነው”፤፤  In 2018, Georgia legislators passed the hands-free law, which states you cannot have your cell phone in your hand or support it with any part of your body. 

 

  1. ከጠጡ ፥ አይንዱ፤  DUI |  ጆርጅያ ውስጥ ሲያሽከረክሩ ፥ በሆነ  ምክንያት ፖሊስ ካስቆመዎትና ፥ ፖሊሱ መጠጥ ካሸተተ ወይም የተከፈቱ የመጠጥ ጠርሙሶችን ካየ ፥ ጠጥቶ በመንዳት ተጠርጥረዋል፤ ፖሊሱ በሚያደርገው የመንገድ ዳር ምርመራ ፥ ሊታሰሩ. ይችላሉ፤ በተጨማሪም በደምዎ ውስጥ 0.08% ወይም ከዚያ በላይ አልኮሆል ከተገኜ፥ በመጠጥ ሃይል አሽከርክረዋል ማለት ነው፤ እስከ ፩ ዓመት ይታሰራሉ፤ መንጃ ፈቃድዎን ለጊዜውም ቢሆን ይነጠቃሉ፤ ፍርድ ቤትም ይቀርባሉ፤ ስለዚህ ከጠጡ ፥ አይንዱ፤  In Georgia. You must be 21 and older to drink. To prevent driving after you've been drinking consider having a designated driver in your group, having a car service or ride share app available to use when you're ready to travel or using public transportation.

 

  1. መኪናዎ ውስጥ ፥ የተከፈቱ የመጠጥ ጠርሙሶችን ፥ ወይም አደንዛዥ ዕፆችን ያስዎግዱ፤.  NO OPEN CONTAINERS | NO POSSESSION OF ILLEGAL DRUGS| ተሳፋሪም ቢሆኑ ፥ የተከፈተ የአልኮል ጠርሙስ ወይም ብልቃጥ ይዘው ቢገኙ ፥ ቅጣትና፡ እንግልት ይጠብቅዎታል፤ በተጨማሪም ፥ ጆርጅያ ውስጥ ፥ መንገድ ላይ ፥ አደንዛዥ ዕፆችን ይዞ መገኜትና ፣ በግልጽ አልኮል መጠጣት ፥ አይቻልም። የመንገድ ላይ ሰካራምነት ፥ በእስርና በገንዘብ ያስቀጣል።  You also cannot drink while walking down the street or handing out on a sidewalk. You also can't drink alcohol in the passenger area of any car. If you have a container of alcohol in the car, make sure it is not accessible፣ ie. put it in the trunk, or locked glove compartment. Don't leave it in an unlocked glove compartment. 

 

  1. ጭፈራ ቤት መሄድ ቢያምርዎ፦  POUR UNTIL 4 |  አካባቢዎን አይረብሹ  ፦ ድምጽዎን ይቀንሱ፣ ለሌሎችም ክብር ይኑርዎት፤ ጆርጅያ የግለሰቦችን ነጻነት እጅግ በጣም ስለምታከር፥ የሌሎችን ነጻነት ከደፈሩ ፥ እስርና እንግልት ይጠብቅዎታልና ፥ ጠንቀቅ ብሎ. መዝናናት አይጎዳም፤  NOISE ORDINANCE | Noise is not allowed Loud Noise is Not Allowed!  ቆሻሻን ባገኙበት መጣልም ፥ ያስቀጣል። NOISE LITTERING | 

 

  1. ለአካለ መጠን ደርሰዋል? LEGAL ADULT | የምሽት መዝናኛ ቤት :  ለመግባት 18 ዓመት፣ አልኮል ለመግዛትና ለመጠጣት ደግሞ ፥ 21 ሊሆንዎት ይገባል፤ You must be at least 18 to attend the adult clubs, and You must be 21 and older to drink.

 

  1. ወሲባዊ ትንኮሳ ፦ Sexual Harassment/Assault/Battery ፥ በእጅጉ የተከለከለና ፥ የሚያስከትለው ሕጋዊ መዘዙም ከባድ ነው፤፤  በጆርጅያ ሕግ፥ ያለሌላኛው/ኛዋ ሰው ፈቃድ ፥ የሌላን ሰው ሐፍረተ ሥጋ፦ በተለይም የሴት ልጅን ዳሌና ጡት ፥ ያለፈቃድ መንካት ፥ እንደ ነገሩ ሁኔታ ፥ ከአንድ ዓመት እስከ ሃያ አምስት ዓመት ፥ የእስራት ቅጣትን ሊያመጣብዎ ይችላል፤ የለመደ ክፉ ልማድ ካለብዎ ፥  ይጠንቀቁ፤ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ፥ በአሜሪካ ብሔራዊ ዳታቤዝ፥ “ወሲባዊ አጥቂ ጥፋተኛ” ፥ ተብለውም ይመዘገባሉ።

 

  1. የመኪና አደጋ ፥ ቢደርስብዎ ወይም ቢያደርሱ. ፦. Personal Injury: Who’s fault? - Georgia has a form of modified comparative fault.

 

  1. በመጀመሪያ ፥ በእጅ ስልክዎ ፎቶ በማንሳት ፥ ማስረጃ ያስቀምጡ፤ Taking pictures with a cell phone is a great way to gather evidence

  2. ፖሊስ ጋ 911 ይደውሉ፤ ስለአደጋው ለፖሊሱ. በተረጋጋ መንፈስ ያስረዱ፤ ፖሊሱ. ሪፖርት እንዲያዘጋጅ ይጠይቁ፤. Call the police when involved in a vehicle crash- Ask the police to report!

  3. በአደጋው ጉዳት ደርሶብዎ. ከሆነ. ፥ ሕክምና  ማግኜት እንደሚፈልጉ ፥ ለፖሊሱ. ያሳውቁ፤ Seek Professional Medical Treatment- First and foremost, if you are injured in any way shape or form, always take care of your health before any legal actions are pursued. 

  4. በአደጋው ለደረሰብዎ ጉዳት ፥ ካሳ ያገኙ. ዘንድ ፥ ሁነኛና ቁምነገረኛ ጠበቃ ጋ ይደውሉ። Call a Competent Lawyer to help you get compensation!

 

የኢትዮጵያውያንን የስፖርትና የባሕል ፌስታል ፥ ለመሳተፍ ፥ አትላንታ ፡ ጆርጅያ ፡ ሲቆዩ ፥ የሕግ ምክርና እርዳታ ቢያስፈልግዎ ፥ (202) 509-2228 በመደወል ፥ ጠበቃ ማንችሎትን ያነጋግሩ፤

 

Law Office of Manchilo Guadie, Inc.

6157 Memorial Drive

Stone Mountain, GA 30083

bottom of page